ይድረስ ለአማራ ህዝብ ጎጃም ቀጠና በተለይም ለጎንቻ፣ እነብሴ እና መካነ ሰላም ወጣቶች:- “”””””””””””””””” በቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ከተቋቋመዉ የዓባይ ሸለቆ ዘብ የተላለፈ ጥሪ…

ይድረስ ለአማራ ህዝብ ጎጃም ቀጠና በተለይም ለጎንቻ፣ እነብሴ እና መካነ ሰላም ወጣቶች:- “”””””””””””””””” በቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ከተቋቋመዉ የዓባይ ሸለቆ ዘብ የተላለፈ ጥሪ:- ——————————– የልዩ ኃይሉን መበተን ተከትሎ በቆራጥ የአካባቢው ተወላጅ ልዩ ኃይል አባላት የዓባይ ሸለቆ ዘብ በሚል የተደራጀው ኃይል ከአንጎት እስከ እነ እነገሽ፣ ከጎሸራ እስከ ወረያ ባለው ቀጠና ያለውን ህዝብ በማንቃት እና በማደራጀት ላይ እያለ በወረዳ ፖሊስ እና ጉጅሊ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ተደርጎበታል:: ለአራት ግዜያት በእነገሽ፣ በበርላይ፣ አባ ሚኒወስ እና ወረያ አካባቢ የተደረገበትን የጉጅሊ እና ፖሊስ ከበባ ሰብሮ ካድሪ የላካቸውን ጉጅሌወች ማርኳል:: የአደረጃጀቱን ዓላማ በበጎ አሳቢ ወንድሞቻችን በኩል ለወረዳ ካድሬወች ለማስረዳት በተደረገው ጥረት እና ተኩስ የከፈተው የመንግስት ኃይል ላይ ባሳየነው አቅም ምክንያት የወረዳ አመራሮች ጉዳዩን ለማቀዝቀዝ ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም የምስራቅ ጎጃም ሸክሞች አብርሃም አያሌው፣ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ እና ፀረ-ህዝቡ ጌትነት አለልኝ አባይ ድልድይ አካባቢ አድማ በታኝ በመላክ ሲያዋጉን አድረዋል:: ለአማራ ህዝብ ነፃነት የተቋቋመው የዓባይ ሸለቆ ዘብ ከሮብ ለሃሙስ አጥቢያ ዛሬ ሌሊት ተኩስ ከፍቶ ያደረውን አድማ ብተና ኃይል ተገቢውን ትምህርት ሰጥቶታል:: ይሁን የዞናችን ህዝብ እድፍ የሆኑት እነኝህ ግለሰቦች መካናይዝድ የመከላከያ ጦር እንዲገባ ለመከላከያ አመራሮች ጥሪ እያደረጉ ይገኛሉ:: በመሆኑም የአካባቢው ወጣቶች ወደ መርጡ ለማርያም የሚወስደውን መንገድ ከሁለቱም አቅጣጫ በመዝጋት እና በአካባቢው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ የትግላችን አካል እንድትሆኑ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን:: እንዲሁም የሬሽን አቅርቦት ችግር ያለብን በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲተባበር ሁሉም በያለበት ጥሪ እንዲያደርግ እናሳስባለን:: “መጭው ታሪክ በእኛ እጅ ይፃፋል” እንዲል ዘመነ ካሴ ታሪካችንን እንፃፍ! እንተባበር! እንበርታ! ግንቦት 03 ቀን 2015 ዓ.ም ዓባይ ሸለቆ

Source: Link to the Post

Leave a Reply