ይድረስ ለአብይ አህመድ:- ሀገራዊ ግዴታህን በመወጣት የሚያልቀዉን የአማራ/አገዉ ህዝብ ከማዳን ይልቅ የመለስን ወንጀል መቼ ቁጠርልን አልንህ? ————- ሸንቁጥ አየለ ——-…

ይድረስ ለአብይ አህመድ:- ሀገራዊ ግዴታህን በመወጣት የሚያልቀዉን የአማራ/አገዉ ህዝብ ከማዳን ይልቅ የመለስን ወንጀል መቼ ቁጠርልን አልንህ? ————- ሸንቁጥ አየለ ——-…

ይድረስ ለአብይ አህመድ:- ሀገራዊ ግዴታህን በመወጣት የሚያልቀዉን የአማራ/አገዉ ህዝብ ከማዳን ይልቅ የመለስን ወንጀል መቼ ቁጠርልን አልንህ? ————- ሸንቁጥ አየለ ——————– የመለሰን ወንጀል በመተረክ የራሱን ወንጀል… አይናችንን ጨፍኑ ብሎ ሊያስረሳን የሚጋጋጠዉ አቢይ አህመድ ህዝብ ሁሌም የሚሞኝ ይመስለዋል::ይልቅስ እንዲህ አይነት ህዝብን የማጃጃል ስራ ከመስራት በአፋጣኝ የሚከተሉትን ሀገራዊ የፍትህ ስራዎች ስራ:- 1–ይልቅስ በመተከል እና በወለጋ እየተከናወነ ያለዉን የአማራ/አገዉ ህዝብ ፍጅት በፍጥነት አቁም 2–ቅድስት ኢትዮጵያ ምድር ላይ የሰዉ ልጅ እሬሳ ክብር ተነስቶስ በግሬደር እንደ ቆሻሻ እንዲጣል ያደረግህበት አካባቢ ላይ አባቶች ፍትሃት እንዲያደርጉ ሰዎችም እንደ እየእምነታቸዉ እንዲቀበሩ አድርግ::አለዚያ ግን የእግዚአብሄርን ቁጣ ጠብቅ::ችግሩ ቁጣዉ ባንተ ብቻ ላይ አይመጣም:: 3–በብዙ ሚሊዮን አማሮች/አገዎች ከመተከል እና ከወለጋ ከሞት ተርፈዉ ከስፍራቸዉ ተፈናቅለዉ በዬቦታዉ በርሃብ ላይ ናቸዉ እና በአስቸኳይ እርዳታ እንዲደርሳቸዉ አድርግ ሌላዉን የፕሮፖጋንዳ ቀልድ እርሳዉ::አንተ በሶስት አመት ዉስጥ አማራን በመፍተጅት እና በማስፈጀት ከመለስ የበለጠ ወንጀል ሰርተሃል::ኦህዴድ/ኦነግም ከህዉሃት የበለጠ ወንጀል ሰርቷል:: የመለስን ሀጢያት ከመቁጠርህ በፊት ከላይ ከ1-3 የተባሉትን ነጥቦች በአስቸኳይ ተግባራዊ አድርግ:: መርሳት የሌለብህ ወያኔ ያን ሁሉ ወንጀል ሲሰራ አሁን በስልጣን ላይ ያላችሁት አንተም ደመቀ መኮንንም እንዲሁም የእናንተ ፓርቲዎች ኦህዴድ/ኦነግም እንዲሁም ብአዴንም ቁልፍ የወንጀሉ ፈጻሚ ነበራችሁ::ለምሆኑ የሚታረዱ:የሚገደሉ እና የሚሰወሩ ሰዎችን እየጠለፈ ለመለስ መንግስት ያቀርብ የነበረዉ አንተ የምትመራዉ ኢንሳ መሆኑን ዘንግተህዉ ነዉ አሁን እንደ አዲስ ወንጀሉን የምታጯጩህዉ? አሁን የመለስን/የህዉሃትን ወንጀል በማጮህ እያለቀ ያለዉን የአማራ/አገው ህዝብ ጉዳይ ለማስረሳት አትሞክር:: አማራ/አገዉ ነን የምትሉ ጋዜጠኞች/አክቲቪስቶች ህዝባችሁ አሁን በባሰ እና በከፋ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን አትርሱት::ስለዚህ ከትናንቱ ወንጀል የባሰ እን አየከፋ ወንጀል በአማራ/አገዉ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ መሆኑን አዉቃችሁ በዚህኛዉ ዘመን ወንጀል ላይ አተኩሩ:: –ከሌላ ነገድ የሆናችሁ ኢትዮጵያዉያን (ማለትም የወያኔ/ኦህዴድ/ኦነግ ፕሮፖጋንዳ የተቀደሰዉን ኢትዮጵያዊነታችሁን ያልነጠቃችሁን ማለቴ ነዉ) ስለሚያልቀዉ የአማራ/የአገዉ ህዝብ ጮክ ብላችሁ መናገር ላይ ብታተኩሩ የራሳችሁንም ነገድ ከእልቂት መከላከላችሁን መሆኑን አትርሱ::ይሄ ጥሪ ግን ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ሀገር ነች ብላችሁ ለምታምኑ ኢትዮጵያዊ ነገዶች ብቻ ነዉ::ወያኔ/ኦህዴድ/ኦነግ ፕሮፖጋንዳ የተቀደሰዉን ኢትዮጵያዊነታችሁን ያልነጠቃችሁን ማለቴ ነዉ::

Source: Link to the Post

Leave a Reply