You are currently viewing “ይድረስ ለጠቅላዩ!” ወጣቱ ገጣሚ ኃይለ ልዑል ምስጋናው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…    ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በተለያዩ…

“ይድረስ ለጠቅላዩ!” ወጣቱ ገጣሚ ኃይለ ልዑል ምስጋናው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በተለያዩ…

“ይድረስ ለጠቅላዩ!” ወጣቱ ገጣሚ ኃይለ ልዑል ምስጋናው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በተለያዩ ጊዜያት በመቅረብ መረጃዎችን ፊት ለፊት በማጋራት የሚታወቀው ወጣቱ ገጣሚ ኃይለ ልዑል ምስጋናው ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ በ13ተኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው ስለሌብነት በጅምላ ፍረጃ፣ ደረጃ መዳቢ ሆነው የዋሉበትን መድረክ በመገምገም ይህን አጭር መልዕክት አስተላልፏል:_ ምድራችን የሌብነትን ሚዛን የምታስቀምጥበት መስፈርት ግልጽ ባለመሆኑ ተሰዳቢው ተሳዳቢው ሆኖ አየን። ክቡርነትዎ እውን ሌባው ማነው? እውነት ይመስክር! እርስዎ በሌብነት የፈረጇቸው የፍትህ ተቋማት ሰራተኞች ሌብነት በሁለት ይከፈላል። 1. በስም እየጠሩ በሌብነት የፈረጇቸው ገሚሶቹ የእርስዎ ዘልዛላ አሰራር የፈጠራቸው እራስ ወዳድ ስግብግብ ግለሰቦች ናቸው። እነኚህ አይነት ኢትዮጵያዊያን የተፈጠሩት እርስዎ ፍቅርን ነቅለው ጥላቻን በመዝራት እና በድህነት ፋንታ ህዝብ ቅነሳ ላይ ስለተሰማሩ ቁጥጥሩ ላልቷል። በመሆኑም ሌብነት የሀገሪቱ ባህል እስኪመስል ድረስ እንዲስፋፋ ካደረጉ በኃላ ንፁህ ለመምሰል መሞከር ህዝብን መናቅ ነውና ወደ ራስዎ ይመለሱ! 2. በእርስዎ አጠራር በሌብነት የተሰየሙት ሌሎቹ የፍትህ ተቋማት ሰራተኞች እርስዎ ከቀበሌ እስከ ቤተ መንግስት ያዋቀሩት ህገ-ወጥ መንግስታዊ መዋቅር በፍትህ ተቋማቱ ስራ ጣልቃ እየገባ ህግ ማስከበር በሚል ማር የተቀባ መርዛዊ አሰራር እያፈነ ባለበት ሠዓት ገለልተኛ የፍትህ ተቋማት እንደገነባ መንግስት መተወኖ በደም የጨቀየ እጅዎትን በክህደት ከመታጠብ ባለፈ ነጻ አያወጣዎትም። ሊያውቁት የሚገባው ነገር ቢኖር የአፋር እና የአማራ ህዝብ መስዋዕትነት የከፈለው እርስዎ እንደ አርበኛ ለመታየት ሲሉ ባሳዩት ቸልተኝነት ነው። ይህ ባለበት እራስን ንፁህ አድርጎ ሌሎችን እንደ ወንጀለኛ መቁጠሩ ኢትዮጵያ እየተሰደበች እናቴ ተሰደበች ብሎ ማጉረምረሙ ህዝብ እየተሰደበ እኔ ተሰደብኩ ብሎ ማለቃቀሱ እራስ ወዳድነት እንጅ ሀገር ወዳድነትዎን አያረጋግጥም! የረሱት ነገር ቢኖር ሌቦች ያሏቸው አካላት ከሰረቁት ንብረት ይልቅ እራስዎ የሰረቁት በእጅጉ ይልቃል! ምክንያቱም ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ፖሊሶች እርስዎ እንዳሉት ቢሰርቁም ገንዘብ ነው። ይልቁንስ የኢትዮጵያ ህዝብ በህይወት የመኖር መብቱን፣ ነፃነቱን እና ስብዕናውን እየተቀማ ያለው በእርስዎ ነው። ለዚህም ዋነኛ መነሻው እራስዎ ህግ አውጪ፣ ህግ አስተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ በመሆንዎ የህገ-መንግስት የበላይነት ተሽሮ የእርስዎ የበላይነት ይተገበራል። ለዚህ ማመሳከሪያው የእርስዎን የተቀባ ንግግር የሚዘግቡ አድር ባይ የመገናኛ ብዙኀን በሰላም እየሰሩ የእርስዎን ድብቅ ሴራ የሚያጋልጡ ታማኝ ህዝባዊ የመገናኛ ብዙኀን ይዘጋሉ። እርስዎ ከዓመት እስከ ዓመት በሚተውኑበት እና ሀገራዊ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ፓርላማ ፊት ያልተጠየቁትን በመመለስ ኮሜዲ ሆነው በዋሉበት ዕለት ያልተደረገ ታሪክ በመፍጠር አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆኗን ወደ ጎን ትተው የአማራና የኦሮሞ ብቻ በማስመሰል አማራ እንደተቃወመ አድርገው በተናገሩት ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት በወለጋ ስለተጨፈጨፉት አማራዎች እንኳን ደስ አለዎት! ለእርስዎ ደስታ ይህ ነውና። የሚያሳዝነው ነገር አዝለው እሹሩሩ በሚሉት እና በኦሮሚያ ክልል ከሚኖረው የአማራ አርሶ አደር የዘረፉትን ኋላቀር መሳሪያ በሚዲያ በማሳየት ከሸኔ ማረኩት ብለው ያወሩት ውሸት ሳያሸማቅቅዎት በጭንቅ ጊዜ የጠሩትንና በሽሽትዎ ዋዜማ የደረሰልዎትን ፋኖን መካድ ተረኝትዎን እንጂ ኢትዮጵያዊነትዎን አያሳይም! ከዚህ በላይ ለእርስዎ ቃል አላባክንም። የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! የምዕራባዊያን ተላላኪ በሆነው ብልፅግና ኢትዮጵያዊ በመሆንህ በምትናገረው ቋንቋ እና በምትከተለው እምነት ሞት ታውጆብሀል! ስለሆነም ዘመን ከጣለብህ የመከራ ቀንበር ለመላቀቅ ውሸት የደም ስሩ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊ ከሚተውነው ቁስ አምላኪው የብልፅግና መንግስት ነጻ ለመውጣት በፍቅር ሆነን ወደ ፈጣሪ በመፀለይ ስጋ ለብሶ የመጣብንን አጋንንት በፅናት መታገል አለብን። ይህንን ካደረግን ይቅር ባይ አምላክ ዝም አይልም! ደግሞም አትጠራጠሩ ብልጽግና ለኢትዮጵያ ትልቁ ጠሏቷ ነው! እግዚአብሔር አስመሳይ ኢትዮጵያዊያንን አስወግዶ እውነተኛ ኢትዮጵያዊያንን ያብዛልን አሜን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply