ይፋት አጉረመረመ! አሥራት ሐምሌ 17/2013/ ዓ.ም ባለግልድሙ፣ ደም መላሹ፣ ቆለኛው ይፋት ሲሰለጥን ውሏል፡፡ በተድበሰበሰና በመንግስት ቸልተኝነት እንደዘበት በገንዘብ የማይገመት በጊዜ…

ይፋት አጉረመረመ! አሥራት ሐምሌ 17/2013/ ዓ.ም ባለግልድሙ፣ ደም መላሹ፣ ቆለኛው ይፋት ሲሰለጥን ውሏል፡፡ በተድበሰበሰና በመንግስት ቸልተኝነት እንደዘበት በገንዘብ የማይገመት በጊዜ የማይለወጥ ጥቃት ሞት መፈናቀልና ውድመት ደርሶብኛል ያለው የይፋት ገበሬና ፋኖ ከዚህ በኋላ ለጠላት ጊዜም ትዕግስትም የለኝም ብሏል፡፡ ከአሥራት የዜና ክፍል ባልደረባ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉ 2 የሸዋሮቢት ሠልጣኝ ወጣቶች እንደተናገሩት ተበድለን እንደበዳይ ሞተን እንደገዳይ የምንቆጠርቀት ዘመን የሚያከትምበትና ጠላት እንዳያቆጠቁጥ ተደርጎ የሚነቀልበት ጊዜ ላይ ነን ብለዋል፡፡ ምኒልክ ብርጌድን፤ሲያነጥፍ እንጂ ሲዘምት የማይታየውን የመንዝ ዘማች፤ እና የሙሉ ሸዋን ፋኖና ሚሊሻ አስተሳስሮ የያዘው “የመሀል አገር መብረቅ”የተሠኘው አዲሱ የብ/ጀ/ ተፈራ ማሞ ኦፕሬሽን ወደ ራያ እያቀና መሆኑንም አክለው ገለፅዋል ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply