ይፋ የተደረገው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ብሄራዊ ክልልን እንዳማያካትት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዘንድሮ ዓመት አካሂደዋለሁ ያለውን ስድስተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28/2013 ዓ.ም እንደሚሆን ቦርዱ የገለጸ ሲሆን የመጨረሻ ውጤት በቦርዱ ይፋ የሚደረገው ደግሞ ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡ይህ ይፋ የተደረገው የምርጫ ሰሌዳ የትግራይ ብሄራዊ ክልልን እንደማያካትት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ቢሮዎችን ለመክፈት የክልል መስተዳደር አከላት ከፍተኛ ትብብር ስለሚያስፈልገው የክልሉ ጊዜያዊ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ጊዜ ስለሚያስፈልገው ነው ተብሏል፡፡በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ መመቻቸቱ ሲረጋገጥ በክልሉ የሚደረገውን ምርጫ ቦርዱ እንደሚያሳውቅ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

**************************************************************************

ዘጋቢ፡ፀጋነሽ ደረጀ

ቀን፡ 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply