ደላንታ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ ሰብአዊ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ ተነገረ

https://gdb.voanews.com/C89E810D-0F3F-4DD9-8647-5850BE17D0A2_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው አካል ይገኝባቸዋል በተባሉት በደቡብ ወሎ ዞን የደላንታ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ አሳሳቢ ሰብአዊ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ተፈናቅለው በወረዳው ዋና ከተማ ወገልጤና የሚገኙ አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ፡፡ 

ተፈናቅለው በወገልጤና ከተማ የተጠለሉ የወረዳው ነዋሪዎች እስካሁን ያገኙት ምንም ዓይነት የዕለት ድጋፍ ያአለመኖሩን አመልክተዋል።

የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባባሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ የደረሰው መረጃ ያለመኖሩን ገልጾ ከሚመለከተው አካል ዝርዝር እንደ ደረሰው ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply