ደሴን ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ እየተሰራ ነው

ደሴን ወደ ቀድሞ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቿ ለመመለስ መንግሥታዊ ተቋማትን ጨምሮ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ሥራ መጀመራቸውን የከተማዋ አስተዳደር ገለጸ። በከተማዋ የሚስተዋለው የኑሮ ውድነት መሻሻል ቢያሳይም አሁንም የመሰረታዊ ምርቶች ዋጋዎች ከእጥፍ በላይ እንደሆነ ኗሪዎች ጠቅሰዋል።

የህወሓት ኃይሎች ገብተውባቸው በነበሩ የምስራቃዊ አማራ ስድስት ዞኖች ውሰጥ አድርሰዋቸዋል የተባሉትን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የሚያጠና ግብረ ኃይል መቋቋሙን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቋል።

ቢሮው በጥናቱ መሰረት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሰው እንዲቋቋሙ ለህዝቡም አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንዲዳረስ ይደረጋል ብሏል፡፡ 

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply