ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተጠራው ሰልፍ ሰዎች እንዳይገኙ ፖሊስ አስጠነቀቀ

https://gdb.voanews.com/49d8c93b-ca34-4386-9660-b86bb1a32429_w800_h450.jpg

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ዛሬ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ እና ጎዳናዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች እየተዘዋወሩ መሆናቸው ተዘግቧል።

ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪርን ለመቃወም ተቃውሞ ሰልፉ ጥሪ ተከትሎ ነዋሪዎች በየቤታቸው በመከተታቸው ጎዳናዎች ከወትሮው ጭር ብለው መዋላቸው ተገልጿል።

መንግሥትን ለመቃወም ዛሬ በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች እንዳይገኙ የሀገሪቱ ፖሊስ አስጠንቅቋል።

ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ በሀገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠይቅ ዘመቻ ሲመራ የቆየው፣ ራሱን ቅንጅት ለህዝባዊ እርምጃ ብሎ የሚጠራው ቡድን የተቃውሞ ሰልፉን የጠራው በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሚመራው ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ዜጎች ለገጠሟቸው በርካታ ችግሮች ተገቢውን ምላሽ አልሰጠም በማለት ነው።

ቡድኑ ስለተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ለፖሊስ በደብዳቤ ማሳወቁን ቢገልፅም የፖሊስ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ዳንኤል ጀስቲን የተቃውሞ ሰልፉ በህዝቡ ዘንድ አለመረጋጋት ስለሚፈጥር ባለስጣናቱ በቸልታ የሚያልፉት አይሆንም ሲሉ መከልከሉን አስታውቀዋል።

ፕሬዚደንቱ ዛሬ በሃገሪቱ ፓርላማ መከፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን የተቃውሞ ሰልፉ አደራጆች ሰልፉን በማካሃድ አቋማቸው እንደጸኑ ትናንት በድጋሚ አሳውቀው ነበር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply