ደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የተጣለውን ሰዓት እላፊ አነሳች

ደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ጥላው የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ከትናንት ጀምሮ ማንሳቷን አስታወቀች፡፡

የአገሪቱ መንግሥት ትናንት ሀሙስ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ፣ በኦሚክሮን ቫይረስ የተቀሰቀሰው አራተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፍተኛው አስከፊ ጊዜ ያለፈ በመሆኑ ከእኩሌ ሌሊት እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ያለውን የእንስቃሴ ገደብ ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም ህዝብ በተሰበሰበት ስፍራ ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ወይም ማስክ ማድረግ ግዴታ ሆነው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ማስክ በሚያስፈልግበት ቦታ ሳያደርጉ መገኘት በደቡብ አፍሪካ ወንጀል መሆኑም በሮይተርስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ የጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመልክተው፣ የአዲስ ተጋላጮች ቁጥር ካለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 16 ጀምሮ በ29.7 ከመቶ ቀንሷል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ወደ 3.5ሚሊዮን ተጋላጮች የተመዘገቡባት ሲሆን፣ 91ሺ የሚሆኑ ሰዎች በወረርሽኙ ሞተውባታል፡፡

ይህ በአፍሪካ ትልቋ ተጠቂ አገር አድርጓታል፡፡

ምንም እንኳ ከፍተኛ የኦሚክሮን ቫይረስ ስርጭት ቢኖርም፣ ወደ ሆስፒታል የሚገባው ሰው ቁጥር እጅግ ዝቀተኛ መሆኑን የመንግሥት መግለጫ አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply