ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተው አዲስ የኮሮና ዝርያ ስጋት ፈጥሯል

https://gdb.voanews.com/1A1917F3-443F-471A-830E-CD43C2D08D8A_w800_h450.jpg

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ስጋት ፈጥሯል።

አዲሱን የቫይረሱን ዝርያ ዐይነት ሳይንቲስቶችአሳሳቢ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ስለምን?ቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ ዐይነቱን እየቀያየረ በመሆኑ እና ጎቴንግ በምትባለው ከሁሉም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባላት ክፍለ ሀገር ወጣቶች ላይ በፍጥነት እየተዛመተ በመሆኑ ነው ተብሏል።

የሀገሪቱ የጤና ሚንስትር ጆ ፓሃላ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ቁጥር በጣም ጨምሯል፥ በአዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።

 አዲሱ የኮሮና ዝርያ ከደቡብ አፍሪካ ወደቦትስዋና እና ሆንግ ኮንግ በተጓዙ መንገደኞች ላይ መታየቱን ሚንስትሩ ገልጸዋል።

የዐለም የጤና ድርጅት  ዛሬ ዐርብ ስብሰባ አድርጎ በደቡብ አፍሪካ ብቅ ያለውን አዲስ ዝርያ ይገመግማል ተብሏል። አዲሱ ዝርያ ቢ 1 1 529 የሚል መለያ የተሰጠው ሲሆን የሚሰብሰቡት የድርጅቱ ባለስልጣናት ከግሪክ ፊደላት መለያ ስም ሊሰጠው ያስፈልግ እንደሆን እንደሆን ይወስኑ ይሆናል ተብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ አዲስ የኮቪድ ዝርያ በደቀነው ስጋት ምክንያት የዐለም የእክስዮኖች ዋጋ አሽቅልቁሏል።

ዛሬ የዐለም የአክስዮኖች ዋጋ ያሽቆለቆለ ሲሆን ነዳጅ  በርሜሉ ከሰማኒያ ዶላር በታች ተሽጧል። ይህ የሆነው ምናልባት ክትባቱ የማይበግረው የቫይረስ ዐይነት ተፈጥሯል በሚል ስጋት መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ገንዘባቸውን ወደ ጃፓን ዬን፥ የስዊስ ፍራንክ እና ወደማያሰጉ ቦንዶች እያዛወሩ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ደቡብ አፍሪካ ላይ ተከስቶ ሆንግ ኮንግ እና ቦትስዋናም ላይ ስለታየው የቫይረሱ ዝርያ ብዙ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ሳይንቲስቶች አዲሱ ዝርያ ባልተለመደ መልኩ ሁለት ዐይነት ዝርያዎችን አደባልቆ የተፈጠረ በመሆኑ በሰውነት የተፈጥሮ መከላከያ የማይሸነፍ እና ከሌሎቹ ይበልጥ ተላላፊ ሊሆን ይችላል ብለው ሰግተዋል።

የብሪታንያ ባለስልጣናት እስካሁን ከታዩት ሁሉ በጣም የሚያሳስብ የኮሮና ዝርያ አድርገው የተመለከቱት ሲሆን ፈጥነው በደቡባዊ አፍሪካ መንገደኞች ላይ ገደብ ጥለዋል።

 ጃፓን፥ ቼክ ሪፐብሊክ እና ጣሊያንም ዛሬ ተመሳሳይ የጉዞ ገደብ አውጥተዋል። የአውሮፓ ህብረት ተመሳሳይ ገደብ ለመጣል ሃሳብ እንዳለው ተመልክቷል።

ኬንያም ከደቡባዊ አፍሪካ በሚነሱ መንገደኞች እንዳይገቡ ባታግድም ከደቡብ አፍሪካ፥ ከቦትስዋና እና ከሆንግ ኮንግ የሚመጡ መንገደኞችን ለአዲሱ ዝርያ የተጋለጡ እንዳይሆኑ እንመረምራለን ብላለች።

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply