ደቡብ አፍሪካ የሊቀጳጳስ ዴሞዝን ቱቱን እረፍት መዘከር ጀምራለች

ደቡብ አፍሪካውያን ትናንት እሁድ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሊቀጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱን የሚዘክሩበትን ሳምንት ጀምረዋል፡፡ 

የኬፕ ታወን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን እስከ መጭው ዓርብ ድረስ ቀትር ላይ የቤተክርስቲያን ደውል በማስማት የጸረ አፓርታይድ ጀግናውን እንደሚዘክር አስታውቋል፡፡ 

ሥርዓት ቀብራቸው በመጭው ቅዳሜ የሚፈጸም መሆኑን ተነገሯል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓትን በመፋለም የሚታውቁት ሊቀጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ እኤአ በ1984 የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ነበሩ፡፡

የደቡብ አፍሪካ የፕሬዚዳንት ዛሬ ሲሪል ራሞፎሳ ትናንት ባወጡት መግለጫ

“የሊቀ ጳጳስ ኤምሪተር ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ነጻ የሆነችውን የደቡብ አፍሪካ ለትውልድ ያወረሱንን ታላላቅ ደቡብ አፍሪካውያንን የምንሰናበትበት ሌላኛው የጀግንነት ምዕራፍ ነው” ብለዋል፡፡

ቱቱ በደቡብ አፍሪካው የአፓርታይድ ጨለማ ዘመን የብርሃን ጮራ ሆነው የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲፈጠርና በነጭና ጥቁር ዘር መካከል ሰላም እንዲስፈን ታላቅ ሚና የተጫወቱ መሆናቸው ተነገሮላቸዋል፡፡ 

አንደበተ ርቱእ መሆናቸው የሚነገርላቸው ዴዝሞንድ ቱቱ በደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ መድረክም በእስራኤል በተወሰዱት የፍልስጤም ይዞታዎች፣ ሰለጾታዊ መብቶች፣ ስለ አየር  ለውጥና በሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ግምባር ቀደም ተሟጋች በመሆን ይታወቃሉ፡፡ 

ፕሬዝዳንት ማንዴላ ዴሞክራሲን ለደቡብ አፍሪካ ባስታዋወቁበት ወቅት የእውነትና የእርቅ ኮሚሽንን የመሩት ሊቀጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply