ደቡብ ኮሪያ፤ ኪም ጆንግ ኡንን “ታላቁ መሪያችን” እያለ የሚያንቆለጳጵሰው ሙዚቃ እንዲታገድ ወሰነች

ደቡብ ኮሪያ የጎረቤቷ ሰሜን ኮሪያ መሪ የሆኑት ኪም ጆንግ ኡን “ቅን አባት” እና “ታላቅ መሪ” ናቸው እያለ የሚያንቆለጳጵሰው ታዋቂ ሙዚቃ እንዲታገድ አዘዘች።

የሴኡል የሚድያ ተቆጣጣሪዎች ይህ የሙዚቃ ቪድዮ የብሔራዊ ደኅንነት ሕጉን የሚጥስ ነው ብለዋል።

ባለፈው ሚያዚያ የተለቀቀው ሙዚቃ በተለይ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል።

“ሙዚቃው ኪም ጆን ኡንን ያንቆለጳጵሳል፤ ከሌሎች በላይ አድርጎ ይስላል” ይላል የደቡብ ኮሪያ ሚድያ ስታንዳርድ ኮሚሽን ሰኞ ያወጣው መግለጫ።

የደቡብ ኮሪያ የብሔራዊ ደኅንነት ሕግ የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ድረ-ገፆችን የሚያግድ፣ መገናኛ ብዙኃን እንዳይሰራጩ የሚያደርግና ለኪም ጆንግ ኡን አገዛዝ የሚያደሉ ድርጊቶችን የሚቀጣ ነው።

‘ፍሬንድሊ ፋዘር’ የተሰኘው ሙዚቃ ሀያ ዘጠኝ ዓይነት ቪድዮ የተሠራለት ሲሆን ሁሉም እንደሚታገዱ የገለጠው ኮሚሽኑ እንዴት የሚለውን ግን ግልጥ አላደረገም።

ሙዚቃው በደቡብ ኮሪያ እንዲታገድ የሆነው ብሔራዊው የደኅንነት አገልግሎት ባቀረበው ጥሪ መሠረት መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጧል።

“ቪድዮው እንደተለመደው ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያለውን ሳይኮሎጂካል ጦርነት የሚገልጥ ነው። የተለጠፈውም ቢሆን በውጭ ኃይል ነው።

ዋና ዓላማው ደግሞ ኪምን ማንቆለጳጰስ ነው” ይላል ተቆጣጣሪው ድርጅት።

ነገር ግን በርካታ ደቡብ ኮሪያዊያን የሙዚቃ ቪድዮው በሀገራቸው መታገዱን ከሰሙ በኋላ ስለሙዚቃው ማወቃቸውን ማሕበራዊ ሚድያ ላይ በሚሰጡት አስተያየት ይፋ አድርገዋል።

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply