ደቡብ ኮሪያ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በአገሪቷ ውስጥ ከውልደት ምጣኔ ይልቅ የሞት ቁጥር አሻቅቦ መገኘቱ አሳስቧታል፡፡

በ2020፤ 275 ሺ 8 መቶ ህፃናት የተወለዱ ቢሆንም ከ2019 ሲነፃፀር በ10 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል ተብሏል፡፡በዚሁ ዓመት ከተወለዱት ይልቅ በሞት ያጣቻቸው ዜጎቿ ቁጥር ከፍ ብሏል፡፡ 307 ሺ 734 ዜጎቿን በሞት መነጠቋ ተገልጿል፡፡ይህ ቁጥር የአገር ውስጥ ሚኒስትሯ መሠረታዊ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ እሳቤ ውስጥ እንዲገባ አስገድዶታል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ሙንዤ ኢን በአገራቸው የውልደት መጠን እንዲጨምር በማሰብ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ያስተዋወቁ ሲሆን ለመውለድ ለሚወስኑ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጎማ ማድረግ ከእቅዳቸው መካከል ይገኝበታል ተብሏል፡፡ይህ የሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡ አገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ከውልደት መጠን የሞት መጠኑ ማሻቀቡ አሳስቧታል፡፡

*****************************************************************************

ቀን 27/04/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply