ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው፡፡

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታው እና በተከታታይ ፕሮግራሞች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሠለጠናቸውን ተማሪዎቹን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከ1 ሺህ 248 በላይ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነው ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው፡፡ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 36 በመቶ የሚኾኑት ሴቶች መኾናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply