ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከደብረ ታቦር እስከ ጋይንት፣ የትግራይ ወራሪ ሃይል የፈፀመውን የማሸበር ጥቃት ተከትሎ በግለሰቦች እና በተቋማት፣ በሀብትና በሰው ላይ የደረሰውን…

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከደብረ ታቦር እስከ ጋይንት፣ የትግራይ ወራሪ ሃይል የፈፀመውን የማሸበር ጥቃት ተከትሎ በግለሰቦች እና በተቋማት፣ በሀብትና በሰው ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን የልየታ ጥናት ይፋ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከደብረ ታቦር እስከ ጋይንት፣ የትግራይ ወራሪ ሃይል በግለሰቦችን እና ተቋማት፣ በሀብትና በሰው ላይ ያደረሰውን የጉዳት መጠን የሚያሳይ የልየታ ጥናት ሪፖርትን ይፋ አድርጓል። ዩኒቨርስቲው እንደገለፀው መረጃው የተሰበሰበው የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭን በመጠቀም ሲሆን ግለሰቦችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ እንዲሁም በአጥኝው ቡድን እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ተወካይ ኮሚቴዎች ጋር ምልከታ በማድረግ ነው፡፡ በጥናቱም አሸባሪው ጁንታ ወራሪ ሃይል በዞኑ በሚገኙ ግለሰቦች፣ የመንግስት ተቋማትና በግል ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ የዘረፋ እና የውድመት ተግባራት መፈፀሙን ለማረጋገጥ መቻሉን ዩኒቨርስቲው በጥናቱ አመላክቷል፡፡ ጥናቱን ያቀረበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች፣ የእርዳታ ድርጅቶች እና ማንኛውም ግለሰብና ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል። አካባቢውን መልሶ በመገንባት ረገድም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ እንድትሰሩ ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡ ሙሉ የጥናት ሪፖርት ሰነዱንም የሚፈልጉ ድርጅቶች እና ልዩ ልዩ አካላት ዩኒቨርሲቲውን በመጠየቅ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል። በተያያዘ ሙሉ የጥናት ውጤት ሪፖርቱን በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ከስእላዊ መግለጫ ጋር ለኢምባሲዎች፣ በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ አለም አቀፍ ተቋማት፣ እንዲሁም ለአገር ውስጥ እና ለውጭ የሚዲያ አካላትና ለሌሎችም የሚያሰራጭ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply