You are currently viewing #ደብረ_ታቦር_/ቡሄ!! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም                    አሻራ ሚዲያ ቡሄ ፣ ጅራፍ ማስጮህ ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድን ነ…

#ደብረ_ታቦር_/ቡሄ!! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ቡሄ ፣ ጅራፍ ማስጮህ ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድን ነ…

#ደብረ_ታቦር_/ቡሄ!! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ቡሄ ፣ ጅራፍ ማስጮህ ፣ ችቦ ማብራትና ሙልሙል ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድን ነው ? በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ነሐሴ ውስጥ እጅግ በርካታ በዓላት ይከበራሉ፡ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በጾመ ማርያም/ ፍልሰታ/ መገባደጃ ላይ የምናከብረው ከጌታችንንና ከአምላካችን ከመድሐኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኝ አበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው /#የደብረ_ታቦር/በዓል ትልቁና ዋነኛው ነው፡፡ ደብረ-ታቦር ጌታችን ያዕቆብ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ካወጣቸው በኃላ በዛ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ዕለት ነው ።ታዲያ ይህን እለትበሀገራችንና ቤተ-ክርስቲያናችን በቀላሉ አክብራው የምታልፍ በዓል አይደለም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ ሥርዓቶችን በመፈፀም አስባው አክብራው ታልፋለች፡፡ ስለዚህም ዛሬ የበዓሉ ዋዜማ ላይ እንገኛለንና እንደ እግዚአብሔር አምላካችን መልካም ፈቃድ በበዓሉ ላይ ትርጉማቸውን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ለበርካታ ጊዜያት የምንፈፅማቸውን ትውፊታዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ምስጢራቸው ምን እንደሆነ እናያለን፡፡ ከስሙ ለመጀመር ያህል የደብረ-ታቦር በዓል በሀገራችን ቡሄ እየተባለ ነው የሚጠራው ቡሄ ምን ማለት ነው? #ቡሄ , ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም ቡሄ ማለት በዓሉ የሚውልበት ወቅት የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት የሚመጣበት ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ” አንድም ቡሄ…..ቡኮ “/ሊጥ” ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋግሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እስኪ የሙልሙል ዳቦን ነገር ካነሳን እርሱስ ሃይማኖታዊ ትርጉም ይኖረው እንደሆነ የታሪኩንም አመጣጥ በዛው እንመልከት #ሙልሙል_ዳቦ , ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡ አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሊነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን ነው። ታዳጊዎች በየደጃፋችን መጥተው “ቢሄ በሉ” ሲሉን ይበሉት ዘንድ ሙልሙል ይሰጣቸዋል። ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችሁበት ሁሉ ሰላምታን ስጡ /ማቴ 10፣12/ብሏልና ሕፃናቱም የሐዋርያት ምሳሌ ስለሆኑ የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን መጽሐፋዊ ነው ማለት ነው። መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆቹም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና ህፃናቱ በሐዋሪያት ይመሰላሉ፡፡ ሌላው ሕፃናትና እረኞችን ስናነሳ ጅራፋቸውንም ማንሳታችን አይቀሬ ነው፡፡ በሀገራችንም ከበዓሉ ቀን መድረስ አንስቶ ለበርካታ ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ጅራፍ ይጮሃል ይሄም በዚህ ታላቅ በዓል ሌላው ገፅታ ነው ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply