ደንበኞች ከትንሳኤ በዓል ዋዜማ ጀምሮ ኃይል ቆጣቢ አጠቃቀምን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አገልግሎቱ ጠየቀ፡፡

በትንሳኤ በዓል ዋዜማና ዕለት የኃይል መዋዥቅና መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመሰጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

እንዲያም ሆኖ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መዋዠቅና መቋረጥ ለመቀነስ በውጭ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በስተቀር፣ ሌሎች ሁሉም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ከዋዜማው ከቀን 7 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ ከዋናው ግሪድ የሚጠቀሙትን ኤሌክትሪክ እንዲያቋርጡ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።

ደንበኞች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት እንዲጠቀሙ ጠይቋል።

የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ ወረፋ ለማስቀረት እንዲችሉ ከወዲሁ የሚበቃቸውን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው እንዲገዙ (ካርድ እንዲሞሉ) አገልግሎቱ አሳስቧል።

ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply