#ደንቢዶሎ በደንቢዶሎ በተማሪወች የበፊቱ ጠባሳ ታሪክ ተደገመ !!!! ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከአማራ ክልል ተነስተው ህዳር 29/03/15 ዓ.ም ወደ ደምቢ…

#ደንቢዶሎ በደንቢዶሎ በተማሪወች የበፊቱ ጠባሳ ታሪክ ተደገመ !!!! ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከአማራ ክልል ተነስተው ህዳር 29/03/15 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎች ከጊምቢ ወደ ደምቢዶሎ እየተጓዙ ሳለ መንገድ ላይ ልዩ ስሙ ጉሊሶ ተብሎ በሚጠራው ቦታ አራጁ እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ የ አማራ ተማሪወችን ብቻ መታወቂያ በማየት ለይተው ከመኪና በማስወረድ ወደ ጫካ ወስደው እንደሰወሯቸው ተገልጿል። ተማሪወቹ ተሳፍረው የመጡበትን ተሽከርካሪም (Odaa bus) አቃጥለውታል ተብሏል ። ከታገቱ ቀን ጀምሮ የልጆቹ ስልክ አይሠራም ሲሉ የተማሪዎች ጓደኞቻቸው እና ወላጆቻቸው ለአሻራ ተናግረዋል። የታገቱት ተማሪዎች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች ተጠቅሷል። 1ኛ) ቤዛዊት ተሾመ 2ኛ)➛ኪሮስ መለሰ 3ኛ) ➛ደጀን ያለው 4ኛ) ብርሀኑ አበባው 5ኛ)➛ቀኑ መለሰ 6)➛ሰይዳ መሀመድ 7ኛ)➛ሲሳይ ጋሻየ 8ኛ)➛ብዙአየሁ አረጋ እና 9ኛ) ➛ማህሌት ዘላለም የሚባሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከአሁንም በፊት የታገቱ የአማራ ተማሪዎች ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወሳል ። ሁሉም Share ያድርገው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply