ዲሽቃ በመስራት ወራሪ ጠላትን ለማጥፋት በፈጠራ ስራ የታገዘው የጠለምት ወጣቶች ተጋድሎ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

ዲሽቃ በመስራት ወራሪ ጠላትን ለማጥፋት በፈጠራ ስራ የታገዘው የጠለምት ወጣቶች ተጋድሎ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠለምት የጀግኖች አርበኞች የነኮሎኔል ሻንበል በየነ መፈጠሪያ ምድር፤ አርበኞች ጠላትን ለማንበርከክ የተፈተኑበት ጠንካራ ህዝብ ተምሳሌት፤ አሁንም ቢሆን ያለማንም ድጋፍና እገዛ በጀግኖች ልጆቿ ብቃትና ቆራጥነት ከትግራይ ወራሪ ሃይል ነፃ የወጣች፤ የበርካታ ወጣቶች ምርጥ ተሞክሮ መፍጠሪያ መገኛ ናት፡፡ በዚህች ወረዳ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይልን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት በሚደረገው የህልውና ትግል የጠለምት ወጣቶችና የጠለምት ህዝብ ያለማንም እገዛ የራሳቸውን የፈጠራ ውጤት ተጠቅመው ከርቀት ጠላትን የሚመታ ዲሽቃ መሳሪያ አዘጋጅተው የጠላትን ቅስም ሰብረዋል፤ ከወረዳቸው አባርረዋል፤ በርካቶችንም ገድለዋል፤ ደማቅ ታሪካቸውን በእጃቸው ፅፈዋል፡፡ ከሰሞኑ ጀግኖቹ ህዳር 08/2014 ዓ.ም የፈፀሙትን ገድል ለመመልከት የስሜን ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ወደ ጅግኖች ምድር ጠለምት አምርቷል፤ ጀግኖች የፈፀሙትን ገድል በአይኑ ቃኝቷል፤ ዘገባውንም እንዲህ አጠናቅሮታል፡፡ የፈጠራ ባለቤቱ ወጣት ሹመት አስማረ እና ወጣት ግርማዉ ከፍያለዉ ናቸው፤ በዕለቱ አግኝተን ቃለ መጠይቅ ያደረግንለት ወጣት ሹመት አስማረ ፈጠራውን እንዴት እንዳከናዎኑት እንዲህ ያስረዳል፡- በሙያየ መካኒክ ነኝ ፣በሚሊሻ ሰልጥኛለሁ ነገር ግን አሁን የተደራጀሁት በጠለምት ፋኖ ነው፤ ጠላት አካባቢያችን ለመውረር አሰፍስፎ ነበር፤ ከሩቅም ይታየን ነበር፤ ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ከሩቅ መምታትና መግደል የምንችለው ስል ለራሴ ጥያቄ አቀረብኩ፤ ድንገትም የዲሽቃ ጥይት አገኘሁ ከጓደኛየ ጋር ሆነን የውሃ ቱቦ በመጠቀም ሰራነው ፤በ6 ጥይት ሞከርነው፤ ይሰራል፤ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ ይሄዳል፡፡ ይህ የጦር መሳሪያ ጠላት በተጠጋን ወቅት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አደረገ፤ ዲሽቃ አላቸው ሲልም ሊጠጋን አልሞከረም፤ በዕለቱም በግንባሩ የጠለምት ብርጌድ በዚህ ዲሽቃ ታግዞ ጠላትን ቀጠቀጠው ከ58 በላይ ገድሏል 8 አቁስሏል፡፡ በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰራነው ዲሽቃ ጥሩ ውጤት ያስመዘገብን ሲሆን በቀጣይ የተሻለና የተሻሻለ መሳሪያ መስራት እንፈልጋለን፤ ምንም እንኳ አሁን ላይ የተጠናከረ ሃይልና ሰራዊት ቢኖርም፤ የበለጠ ሰርተን ወራሪውን የትግሬ ቡድን ለአካባቢያችን ብሎም ለሃገራችን ስጋት እንዳይሆን የማንፈጥረው ስራ የለም፡፡ መንግስት ሊያበረታታንና ሊደግፈን ይገባል፤ ለጠላት አናንስም እስካሁንም ባለመደራጀታችን ነው ለዚህ የደረስነው እንጅ የአማራ ህዝብ ከተደራጀ አይደለም ለትግሬ ለአለም ስጋት ነው፡፡ ወጣቶቻችንም የበለጠ ሙያ ለማግኘት መከላከያ ተቀላቅለን በቂ ስልጠና በመውሰድ እነባለከዘራው ኮ/ል ሻንበል በየነ የሚፈፅሙትን ጀብዱ እኛም ልንደግመው ይገባል፤ የሃገራችን ነቀርሳ ነቅለን ልንጥለው ይገባል፡፡ ብሎናል። ዘገባው የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply