ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት ከ1.5ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ።በቤት ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኝው ዲኤምሲ ሪል እስቴ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/GifpmdbghK88hpqanP-Qmb4A9tr0LiEBNuwhXtSxzAEwTpvywfUFoxmdgDIKdFxOcl0s6AHMWQ2ufMLXZd2mi9SuWXct1RAofy2KQyeuJMjrsNIFpbULIGiX8chXBxTPM2GINiq7AccSmJl7MubqqEx2PpnYd1xH3RBS8lQQXbHzg2Dq_ZxxEd_Bfz4AIMC_58Z8voBc7xiXIDQ2rHD5Z0HYPZoK4LPWbm8xiE4urF4-JhKnMP-qAero6Dg23y9oxzcQ19TssuGBsX-MpaDw2sOuF1x8u87y2Tk6SOi5wcn8UsRpi7epCFKwgUrozPpGPFrkNGxNEXvqTikzJitNZw.jpg

ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት ከ1.5ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ።

በቤት ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኝው ዲኤምሲ ሪል እስቴት በአሉን ምክንያት በማድረግ ለ900 አረጋዊያን የምሳ ግብዣ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል።

ላለፊት 27 አመታት በመንገድ በኮንስትራክሽን እና በቤት ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘው ዲኤምሲ ሪልእስቴት ከዚህ በተጨማሪም ለሜቄዶኒያ 250 ብርድ ልብሶችም ድጋፍ አድርጓል።

በሜቄዶንያ በኩል ከድርጅቱ ቤት ለመግዛት ለሚመጡ ደንበኞች እስከ አምስት በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግ ነው የተነገረው።

ደርጅቱ በተለያዩ ጊዜያቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው።

ዲኤምሲ ሪልእስቴት ለመቄዶንያ ያደረገው የአይነት ድጋፍ በገንዘብ ከ1.5ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ተብሏል።

ድርጅቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ባሁኑ ሰአት ከ7ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ተረጂዎችን በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፤ ሻሽመኔ፣ አድዋ እንዲሁም ባህርዳር ጨምሮ በሌሎች 27 ከተሞች ውስጥ እየስራ ይገኛል።

በቀጣይ ወሊሶ፣ በሱልልታ፣ ሰበታ፣ ደብረ ብርሃን፤ ሆሳዕና፣ ዲላ፣ ጂግጂጋ፣ እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችን ለመስራት ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተነግሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply