ዳሸን ባንክ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበር በእንጦጦ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናወነ፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ…

ዳሸን ባንክ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበር በእንጦጦ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናወነ፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የዛሬው ችግኝ ተከላ ባንኩ በአካባበቢ ጥበቃ ዘርፍ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበር ለተከታታይ አመታት በእንጦጦ ተራራ ላይ ሲያከናውን የቆየው ችግኝ ተከላ ውጤት ማስመዝገቡንም አብራርተዋል፡፡

ባንኩ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ እያከናወነ ያለው ተግባር የእንጦጦ ተራራን ስነ- ምህዳር ለማስቀጠል የድርሻውን እያበረከተ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለት በርካታ ሃገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ከዚህ ቀደም በእንጦጦ ተራራ ላይ የተከላቸው ችግኞች የፀድቀት መጠናቸው ከፍተኛ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ ባንኩ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ጋር በመተባበር በየአመቱ የሚተከሉ ችግኞች ክብካቤ እንዲያገኙና እንዲፀድቁ እያደረገ ይገኛል ፡፡

በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ ከዋናው መስሪያ ቤት፣ ቀጠና ፅህፈት ቤቶችና ቅርንጫፎች የተውጣጡ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ በዘላቂ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ራሱን የቻለ ፖሊሲ በመንደፍና መምሪያ በማቋቋም እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ መምሪያ የባንኩ የቢዝነስ ዕንቅስቃሴዎች የፓሪስ ስምምነትን፣ ዘላቂ የልማት ግቦችንና ሌሎች ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶችን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡

ለዚህም ይረዳው ዘንድ ባንኩ በአየር ንብረት ለውጥ፣ዘላቂነትን ታሳቢ ባደረገ የፋይናንስ አቅርቦት፣ ዘላቂና ደህንነቱ በተጠበቀ ክዋኔና በአካባቢያዊ ትግበራ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ቋሚ አባል ሲሆን ለማህበሩ የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply