የባንኩ ባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጉባኤ በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ተካሂዷል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን፣ ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ችግሮች የነበሩበት ዓመት ቢሆንም፣ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት በበርካታ ዘርፎች ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል።
ባንኩ ተጨማሪ 23.6 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ያስታወቀ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሃብቱም 144.6 ቢሊየን ብር እንዳደረሰ ተገልጿል።
ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 5 ቢሊየን ብር ትርፍ እንዳገኘም አስታውቋል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት 253 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መክፈቱንና አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ835 በላይ ማድረሱን አስታውቀዋል።
ከ5.2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ያሉት ዳሸን ባንክ ተጨማሪ 23.6 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን የገለፀ ሲሆን አጠቃላይ ሃብቱን 144.6 ቢሊየን ብር ማድረስ ችያለሁ ነው ያለው፡፡
ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት ያገኘው 5 ቢሊየን ብር ትርፍ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ319 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡
ዳሸን ባንክ በአገሪቱ የግል ባንኮች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን 40 ሚሊየን ዶላር የውጭ ብድር በቅርቡ ማግኘቱን ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ይህም በዘርፉ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ከመቅረፍና የግብርና ምርት ወደውጭ ከመላክ አንፃር ከፍተኛ አውንታዊ ሚና እንደሚኖረው አስገንዝበዋል።
በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post