ዳሸን ባንክ የአመቱ ቀዳሚ ባንክ በመሆን “ዘ ባንከር” መፅሄት የሚያበረክተውን ሽልማት ተቀበለ፡፡

ዳሸን ባንክ እ.ኤ.አ በ2022 “ዘ ባንከር” የተሰኘና በፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ስር በሚታተመው መፅሄት ቀዳሚ በኢትየጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ቀዳሚ ሆኖ በመመረጥ ሽልማት መቀበሉን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ሽልማቱን የተቀበለው የዘንድሮውን ጨምሮ ለ12ኛ ጊዜ ሲሆን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በእንግሊዝ ዋና ከተማ ሎንዶን በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ዘርፍ በተለይ ባለፈው ዓመት ያሳየው እመርታ ለሽልማት አብቅቶታል፡፡

ባንኩ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት ዘርፍ ያከናወናቸው ተግባራት እንደ ኢትዮቴሌኮምና በፋይንንስ አገልግሎት ዙሪያ ከሚሰሩ ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የመስራት አቅም ከመፍጠሩም በላይ አነስተኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን ለማስፋት አስችሎታል፡፡

ዳሸን ባንክ በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋለው ዕድገት፣ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱና የካፒታል ገበያ መቋቋም እንዲሁም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭዎች በባንክ አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት የሚፈጥሯቻን እድሎች በማጤን ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማምጣት እየሰራ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ባለፈው ዓመት ፍላተርዌቭ፣ ቱንስና ኤምኤፍኤስ ከተሰኙ በአፍሪካ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡

ባንኩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማስፋትና ለመፍጠር የሚያስችለውን በግል የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጀመሪያው የሆነውን ደረጃ 3 ግዙፍ የዳታ ማዕከል ያስገነባውም ባለፈው በጀት ዓመት ነበር፡፡

ዳሽን ባንክ ከ700 ባለይ ቅርንጫፎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመክፈት መደበኛና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞቹ በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply