ዳሸን ባንክ የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ሽልማት ተቀበለ።ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/qD8i2IAA9XYd4du5g9pOcHhyeZXQWZ5r0UtdxREN1YZmxTGWAMqhgNcHWkdCdpKr4ZYdeTDzztCW36xXmIBfNf3D_6Vf8kjHKwfjlrsvF5nTovgxS-2E-7dqydHLCVbUHZ9iQhu6Nj-tVYjxhmyNr1avl279xCcwdhSfuZgzmc3EE3Md5oN53IhZMLgB0cV4bUMWf69CFGq-1yyxOY4Lk2H6zCzpoBFoB-7H3zxPpwZ6y2IzxfenlmmR6j7p2vil5oOFZhbXpSv-qB1ZEkaGSvnjSc6mgzaevcT3i2PZXxFIGerw3D4VzJeDUXdR-nXzEcxSMYoAZ21k9VJfrlPp0A.jpg

ዳሸን ባንክ የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ሽልማት ተቀበለ።

ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ዘርፍ ለዳሸን ባንክ “Outstanding Global Trade Finance Program Issuing Bank” ሽልማት መስጠቱን ስናበስር በደስታ ነው ብሏል ባንኩ፡፡ 

ሽልማቱ የተሰጠው ኮርፖሬሽኑ  8ኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በስፔን ሀገር ባርሴሎና  ከተማ ባደረገው ጉባኤ ላይ ነው፡፡ 

በተያያዘ ዜና ዳሸን ባንክ በሀገሪቱ ለሚገኙ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት የፋይናንስ አገልግሎት የመስጠት አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግና የፋይናንስ ተደራሽነትን በተሻለ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን  ጋር ተፈራርሟል፡፡ 

ስምምነቱን ሩዋንዳ ኪጋሊ ተገኝተው የፈረሙት የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው፡፡

ስምምነቱ ዳሸን ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን እና አካታችነትን ይበልጥ እውን ለማድረግ አቅም የሚጨምርለት ሲሆን በጥቃቅን፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም በግብርና ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች በተለይ በሴት ባለቤትነት የሚመሩትን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply