ዳሽን ባንክ እስከ 7 መቶ ሺ ብር    በዱቤ መግዛት የሚያስችል አገልግሎት ጀመረ።    ዳሽን ባንክ”ዱቤ አለ”  በተሰኘው  መተግበሪያ ሸማቾች ፣አምራቾች እና አገልግሎት  አቅራቢዎች   በ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/UlzC3IxKJe0T-cn67_abUq90g-fXXa2RZ3YXZ5CL-X-9cQh9i41sCluNBfxMdYfRDphOffT6eKeSNIIKJobmpR3VN4UoFgqwRvKjBmgFcYmdqB1fnIG06GSTLbwb642eELM9BttAfHJbIWEqzINMmc2SEFLNw-0Kjtmyx4quPSbLDDQNSu0YmDCv39ZaXNHK7uKPN_Q86tHSrIsQ_KHG0hxrcY0p3EgMjVMdh1mLMTaRpnhEA-aDBbh8DQUmf9sBbKBmSRNc-Tm4qXOBIOjs8Gz6z_HduU_v4Usg9J7xWCIVEXcZd4m40Q629Kzd3kRcPySkVqlgjD9WlX5x-Ne9Hg.jpg

ዳሽን ባንክ እስከ 7 መቶ ሺ ብር    በዱቤ መግዛት የሚያስችል አገልግሎት ጀመረ። 

  ዳሽን ባንክ”ዱቤ አለ”  በተሰኘው  መተግበሪያ ሸማቾች ፣አምራቾች እና አገልግሎት  አቅራቢዎች   በዱቤ  የሚገናኙበትን ዘመናዊ የግብይት መተግበሪያ  ይዞ መቷል።

ባንኩ  በትናንትናው  እለት  ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ እና ኢትዮጵያ  ውስጥ  ከሚገኙ  የተለያዩ  ምርትና አገልግሎት  የሚያቀርብ የንግድ  ድርጅቶች  ጋር  በጥምረት  ያሰራው  “ዱቤ አለ “የተሰኘው  መተግበሪያ ወደ ስራ ገብቷል ።

” በዱቤ አለ”መተግበሪያ  ሸማቾች በፈለጉት  ጊዜ    ያሻቸውን  በዱቤ በመግዛት በተሰጣቸው የጊዜ  ገደብ መክፈል የሚችሉበት አሰራር  ነው።

ይህ አገልግሎት ዳሸን ባንክ ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ጋር በመተባበር ህብረተሰቡ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና በርካታ አገልግሎቶችን  በ3 ወር በ6 ወርና በ12 ወር በሚመለስ ዱቤ በወለድና ያለወለድ መግዛት የሚያስችላቸውን አማራጭ ይዞ መቷል ።

ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕ ስቶር በማውረድ ለአገልግሎቱ መመዝብ ይችላሉ ተብሏል ።

ከተመዘገቡ በኋላም ወደ ዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በማምራት የዱቤ ገደብ ማስፈቀድና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply