ዳሽን ባንክ  እና ኩሪፍቱ ሪዞርት አዲስ የክፍያ መፈፀሚያ   አገልግሎትን  አስጀመሩ። ዳሸን  ባንክ እና ኩሪፍቱ  ሪዞርት የስጦታ ካርድ እና  በእጅ ሰዓት አማካኝነት ክፍያ መፈጸም  የሚያስ…

ዳሽን ባንክ  እና ኩሪፍቱ ሪዞርት አዲስ የክፍያ መፈፀሚያ   አገልግሎትን  አስጀመሩ።

ዳሸን  ባንክ እና ኩሪፍቱ  ሪዞርት የስጦታ ካርድ እና  በእጅ ሰዓት አማካኝነት ክፍያ መፈጸም  የሚያስችል አገልግሎት  መስጠት ጀምረዋል።

ዳሽን ባንክ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መገበያያ አንደኛው  የስጦታ ካርድ  ሲሆን   ይህ የስጦታ ካርድ ደንበኞች   ከዳሽን ባንክ   ወደ ስጦታ  ካርዱ ሂሳብ  በመሙላት  የኩሪፍቱ ሪዞርት አገልግሎቶችን የሚገበያዩበት  እና ለሌሎች ስጦታ  የሚሰጡት መገበያያ  ካርድ ነው።

በተጨማሪም በሰዓት መልክ የተዘጋጀው   ( Wrist Band) የክፍያ ማስፈፀሚያም    በዳሽን ባንክ   በኩል ሂሳብ ተሞልቶበት የኩሪፍቱ አገልግሎቶችን  መገበያየት የሚያስችል በ (Water proof) መንገድ የተዘጋጀ  መገበያያ ነው።

የዳሽን ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ ዮሀንስ ሚሊዮን በዚህ ማስጀመሪያ ባደረጉት ንግግር የእነዚህ የክፍያ መፈጸሚያዎች በአገልግሎት ላይ መዋል የክፍያ ስረዓትን ከማዘመን እና ከቀላልና ከማድረግ ባሻገር ደምበኞች ባንኩ በየጊዜው የሚሰጠው ተመላሽ ገንዘብ እና ቅናሽ (cash backs and discounts) ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥርላቸዋል ብለዋል።

ይህን ካርድ ለመጠቀም ደንበኞት የሂሳብ ቁጥር ሳይኖራቸውና ስማቸው በካርዱ ላይ ሳይጠቀስ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል ።

ይህ  የስጦታ ካርድ እና በእጅ የሚታሰረው የክፍያ መፈጸሚያ በኩሪፍቱ እንጦጦ እና ቢሾፍቱ፣ በቦስተን ዴይ ስፓ እንዲሁም በተመረጡ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች እንደሚገኙም  ተነግሯል።

አገልግሎቶቹ በየጊዜው በየትኛውም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ የሚሞሉና  ጊዜያቸውን ሲጨርሱ የሚታደሱ  ናቸው።

ዳሽን ባንክ አዳዲስ እና በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ የባንክ አሰራሮችን ለደምበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል ፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

Source: Link to the Post

Leave a Reply