ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት ድጋፍ እንዲያገኙ እድል የሚያመቻች አውደ ጥናት በሬው እለት ተካሂዷል፡፡አውደ ጥናቱ በዋናነት ስር የሰደደ ድህነት መረጃና ማስረጃዎች ላይ የሚመክ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/FVzwYM83VgIyD5MbggIWurzmjWIdIwjncjNZ-1OxczOzS0ZTr519l7KcKoukf-bIpRavlU256P0d2NOHtNco1s4X_PRjtZ-QWRXeQAgfqsDHQzW0ui9_bKm-aonRgvdf51vAFxe4xI-WLqLdIXf-Vm4FwkU1ycy1A9XCeYETv2ZmE4PXgOV4Wiqgmo0ZCvwjwi5ZSSaSU9KFmW3p5oK6pvCx_JDO0nPMdaOF_cmsg_DwWOAwg2JAETZkBkqxknf4PZpi_MNK6yxO2O0p0RpsO7HUcWL6fvLwEvoTwoIrmq23ADfNydNPjUMhkaFgVGAnw4EZQ9xVwbqYm9JoesaRIQ.jpg

ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት ድጋፍ እንዲያገኙ እድል የሚያመቻች አውደ ጥናት በሬው እለት ተካሂዷል፡፡

አውደ ጥናቱ በዋናነት ስር የሰደደ ድህነት መረጃና ማስረጃዎች ላይ የሚመክር ነበር፡፡

ኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት የተሰኘ ተቋም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስር የሰደደ ድህነት መረጃና ማስረጃዎች ላይ የሚመክር አዉደ ጥናት አካሂዷል፡፡

አዉደ ጥናቱ ከኮርኔል ፣ ኮፐን ሃገን እና ሳዉዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የሚመራ ነዉ፡፡

አዉደ ጥናቱ ‹‹ዲፕ ቻሌንጅ ፈንድ›› የተሰኘ አነስተኛ እና መካከለኛ የገንዘብ ድጋፍ በድህነት ቅነሳ ላይ ለሚሰሩ የአገር ዉስጥ ተቋማት እና ተመራማሪ ግለሰቦች ለሚሰጠዉ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ፕሮግራም ነዉ፡፡

ይህ አዉደ ጥናት ባለድርሻ አካላት እና ተመራማሪዎች እንዲገናኙ እና ሀሳብ እንዲለዋወጡ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከዚህ አዉደ ጥናት በኋላ ከሰኔ እስከ ሃምሌ ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ደግሞ ድህነት ቅነሳ ላይ ለሚሰሩ የአገር ዉስጥ ተቋማት እና ተመራማሪ ግለሰቦች የገንዘብ ድጋፉ የሚሰጥበት መርሃ ግብርም በይፋ ይጀመራል ተብሏል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply