
ድምጻዊ ቃልአብ ሙሉጌታ “ይቅናሽ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለሕዝብ እንደሚያደርስ ታውቋል::
13 ሥራዎችን ያካተተው አልበሙ ሦሥት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በዜማና ግጥም ዳዊት ተስፋዬ፣ እሱባለው ይታየው የሺ፣ ሚኪያስ ሞገስ፣ አሰግድ እሸቱ፣ ቤቢ ሞኢሳ፣ እና ሙሉዓለም ታከለ ራህዋ ተሳትፈውበታል:: ሙዚቃዎቹን ደግሞ ሚኪያስ ሞገስ፣ ርኆቦት ሽመልስ፣ ታምሩ አማረ፣ እና እስራኤል መስፍን ያቀናበሩ ሲሆን ማስተሪንጉ በአበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ተከናውኗል::
አልበሙ ቃልአብ ሙሉጌታን ጨምሮ በርካታ ድምፃውያን፣ የዜማና የግጥም ደራሲዎች፣ እንዲሁም ሙዚቃ አቀናባሪዎች በጋራ በመሠረቱት ፊርማ የቲዩብ ቻናልና በዋነኞቹ ዓለም-አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ሁሉ እንደሚሰራጭ ታውቋል::
Source: Link to the Post