You are currently viewing ድምጻዊ አበበ ካሴ በጸና መታመሙን በመግለጽ “አሳክሙኝ” ሲል ጥሪ አቀረበ፤ ለህክምና የሚሆን አስቸኳይ ወገናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 13 ቀን…

ድምጻዊ አበበ ካሴ በጸና መታመሙን በመግለጽ “አሳክሙኝ” ሲል ጥሪ አቀረበ፤ ለህክምና የሚሆን አስቸኳይ ወገናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 13 ቀን…

ድምጻዊ አበበ ካሴ በጸና መታመሙን በመግለጽ “አሳክሙኝ” ሲል ጥሪ አቀረበ፤ ለህክምና የሚሆን አስቸኳይ ወገናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በድምጻዊነት፣በሽለላ እና በፉከራ ጭምር የሚታወቀው ጀግናው አበበ ካሴ በጸና መታመሙን በመግለጽ ለህክምና የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል። ድምጻዊ አበበ ከአሁን ቀደም የተሻለ ህክምና ህክምና ያስፈልግሃል በሚል ወደ አዲስ አበባ ኮርያ ሆስፒታል ሪፈር የተደረገ ቢሆንም የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ከ400,000 ብር በላይ በመሆኑ ለመክፈል አቅሙ አልፈቀደም። ድምጻዊ አበበ ካሴ በጎንደር ጠገዴ ፣ ወልቃይት እና በተለያዩ አካባቢዎች በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጦርነት ጊዜም ጭምር ፋኖ ሆኖ በመታገል እና ግንባር ላይ የተሰለፉ ታጋዮችን በማበረታታት ይታወቃል። በብዙዎች ዘንድ በትግል አነቃቂ ስራዎቹ ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፈው አበበ መጋቢት 11/2014 የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ባደረገው ታሪካዊ ጉባኤው ላይ ተገኝቶ በማንጎራጎር “እግሬን ክፉኛ አሞኛል፤ አሳክሙኝ!” ሲል ተደምጧል። ድምጻዊ እና የነጻነትን ታጋይ አበበ ካሴን መርዳት ለምትፈልጉ:_ የስልክ አድራሻ:- 0912188182 አበበ ካሴን ደውሎ ማናገር ይቻላል ! የንግድ ባንክ አካውንት አበበ ካሴ ተገኘ 1000018881137 መጠቀም የምትችሉ መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply