ድሬዳዋ ላይ የተጀመረው የሳፋሪ ኮም አገልግሎት ደንበኞቹ አስተያየት

https://gdb.voanews.com/09ae0000-0a00-0242-002d-08da8c541917_tv_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው የግል ተቋም ደንበኛች አገልግሎቱን እየተጠቀሙ ነው። ሳፋሪ ኮም የተባለው ይሄው የመጀመሪያ የግል ተቋም የሙከራ አገልግሎቱን በቅድሚያ የጀመረው በድሬዳዋ ነው።

ባለፈው ሰኞ የተጀመረው አገልግሎት ከኢትዮ-ቴሌኮም ወደሳፋሪ ኮም ሲደወል ከሚያጋጥመው ችግር በስተቀር በተሳካ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ደንበኞች ተናግረዋል።

የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የቀረቡበት ዋጋም ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር ተቀራራቢ መሆኑን የሳፋሪ ኮም መግለጫ ያመለክታል።

አዲስ ቸኮል የሳፋሪኮምን የመጀመሪያ ደንበኞችን አነጋግሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply