ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሲመሩ ከቆዩት ፍስሐ ጥዑመልሳን ጋር ተለያይቷል፡፡

ድሬዳዋ ከተማን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ያለፉት ወራትን ቡድኑን እየመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ፍስሐ ጥዑመልሳን በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

ከ2010 ጀምሮ ለድሬዳዋ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት አሰልጣኝ ፍስሐ፤ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይን በመተካት ዋና አሰልጣኝ ሆነው ቡድኑን ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው።

‘‘ክለቡ በሚፈልገው ደረጃ ውጤት አልመጣም’’ በሚል አስቀድሞ ለአሰልጣኙ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አድርሷቸው የነበረ ሲሆን፤ ቡድኑን ለቀጣይ ጨዋታ ለማዘጋጀት ባህር ዳር ከተማ ባሉበት ወቅት በክለቡ በኩል ጥሪ ተደርጎላቸው በትናንትናው ዕለት ወደ ድሬዳዋ በመመለስ ዛሬ ከክለቡ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህም በስምምነት ለመለያየት መስማማታቸው የታወቀ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም በቀጣይ ቀናት ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ እንደሚሾም ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply