ድርቅን ለመቋቋም የተቀናጀ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አንድ ባለሞያ ተናገሩ

https://gdb.voanews.com/DD608531-EAD1-451F-BD85-7E4DB2C43FA1_cx0_cy27_cw0_w800_h450.jpg

በያዝነው ዓመት በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን እና በአጎራባቹ የሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በደረሰ ድርቅ ቁጥራቸው በ10 ሺዎች የሚገመት እንስሳት መሞታቸውን ተነግሯል።  

“ለመሆኑ በእነኚህ አካባቢዎች የሚከሰተው ተደጋጋሚ ድርቅ መንስኤው ምንድን ነው? የአጭርና የረጂም ጊዜ መፍትሔዎቹስ ምንድን ናቸው? አሁንስ ምን እየተደረገ ነው?” በሚሉትና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የግብርና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች አጥኚውን ረዳት ፕሮፌሰር በላይ ጩፌን ጠይቀናል።

ረዳት ፕሮፌሰር በላይ ጩፌ ለአሜሪካ ድምጽ እንደገለጹት የአርብቶ አደር አካባቢዎች ለተደጋጋሚ ድርቅ የተጋለጡ እንደሆኑና ይህን በዘላቂነት ለመቀነስ ከልማዳዊ አሠራሮች ባለፈ በአጭርና በረዢም ጊዜ ሊተገበሩ የሚገቡ መፍትሔዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply