ድርቅ በትምህርት ላይ የደቀነው መሰናክል

https://gdb.voanews.com/019e0000-0aff-0242-23fa-08da8ab41982_tv_w800_h450.jpg

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ በዚህ ዓመት በደረሰው ድርቅ ምክንያት ከሰባት ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምሕርታቸውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን የዞኑ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ተማሪዎቹ ዓመቱ የተስተጓጎለባቸው ቤተሰቦቻቸው ለእንስሣቱ ግጦሽና መኖ ፍለጋ ስለሚንቀሳቀሱ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤል አመልክተዋል።

ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች አዲሱ 2015 የትምህርት ዘመንም እያሳሰባቸው መሆኑን ኃላፊው ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁ ሲሆን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ደግሞ ምላሽ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply