
“ድርጊቱ መንግሥት ባለበት ሀገር በመከናወኑ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው።” የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሚመራው የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በዛሬው ዕለት ኢ-ሕጋዊ በሆነ መልኩ የተከናወነውን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ሀገረ ስብከቱ በመግለጫው የጥምቀት በዓል በፍጹም ደስታና ክርስቲያናዊ አንድነት በተከበረበት ማግስት አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን ሊያስፋፉ ቃል የገቡ ሊቃነ ጳጳሳት ሲመተ ኤጲስ ቆጶስ በማከናወናቸው ማዘኑን ገልጿል። ድርጊቱ መንግሥት ባለበት ሀገር በመከናወኑና በሕገ መንግሥት የሚያስጠይቅ በወንጀል በመፈጸሙ በሕግ እንደሚጠይቃቸውና እርምጃም እንደሚወስድባቸው እንደሚያምን ተናግሯል። በሀገረ ስብከቱ ያሉ ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ተማሪዎች በጸሎት እንዲጸኑና አንድነታቸውን እንዲያጸኑ አሳስቧል። አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
Source: Link to the Post