#ድባቴ እንዴት መከላከል ይቻላል?ከሳምንታት በላይ የሚቆይ ደስታ የማጣት የመደበት አይነት ስሜት ድባቴ መሆኑ ይነገራል፡፡ ድባቴ የእለት ተዕለት የሰዎችን ህይወት የሚረብሽ እና ጫና የሚያሳድር…

#ድባቴ እንዴት መከላከል ይቻላል?

ከሳምንታት በላይ የሚቆይ ደስታ የማጣት የመደበት አይነት ስሜት ድባቴ መሆኑ ይነገራል፡፡ ድባቴ የእለት ተዕለት የሰዎችን ህይወት የሚረብሽ እና ጫና የሚያሳድር መሆኑ በባለሞያዎች ዘንድ ሲነገር ይደመጣል፡፡

የስነ ለልቦና ባለሞያ የሆኑት ሄኖክ ዩሃንስ ድባቴ ሊከሰት የሚችለው በተፈጥሮ ፣ ስነልቦናዊ እና በማህበራዊ አሉታዊ ጉዳዮች መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በተፍጥሮ ድባቴ የሚከሰተው በሰውነት ውስጥ ያሉ ሆርሞኖች እኩል አለመሆን እና በቤተሰብ ይህ አይቱ እክል ካለ መሆኑ ጠጠቁሟል፡፡

በማህበራዊ ጉዳዮች ደግሞ ከገንዘብ እጦት፣ በፍቅር ግንኙነት ላይ በሚፈጠሩ አለመግባቶች ሲሆን፤ ሰዎች ለራሳቸው ባላቸው ዝቅተኛ የሆነ በራስ መተማመን እና ስነልቦናዊ ጉዳቶች ድባቴ ሊከሰት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
#ለድባቴ የአእምሮ እክል እንደ መንሰኤ የሚጠቀሱት፤

• በልጅነት የዕድሜ ክፍል ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች ተጋላጭ መሆን
• የትዳር ፍቺ እንዲሁም በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶች አና የትዳር አጋርን የህይወት ማለፍ
• የወላጅ ወይም የቅርብ ሰውን በሞት ማጣት
• ጾዊ ጥቃት
• ብቸኛ መሆን
• ከአውንታዊ ይልቅ አሉታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ
• ከዚህ ቀደም የነበረ የድባቴ ስሜት መኖር
• አካላዊ የአንጎል ሕመም
• በቤተሰብ ውስጥ ይህ አይነቱ ችግር ካለ
• አልኮል መጠጦችን ማዘውተር እና እደንዛዥ እጾች መጠቀም ለድባቴ እንደ መነሻ ምክንያት ተጠቃሽ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
የድባቴ ምልክቶች እንደየሰው ሊለያይ እንደሚችል ይገለጻል፤
• ተስፋ መቁረጥ እና መተከዝ
• በየዕለቱ ሊሚከናወኑ ድርጊቶች ፍላት ማጣት
• ከዚህ ቀደም ሊያዝናና እና የደስታ ምክያት የሆኑ ጉዳዮች ላይ ደስታን ማጣት
• ምክንያትቱ ባለታወቀ ሁኔታ የሰውነት ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር፣
• እረጅም ሰዓትን በእንቅልፍ ማሳለፍ ወይም የእንቅልፍ እጦት ችግር
(የእንቅልፍ መዛባት)
• እራስን የመውቀስ ሁኔታዎች በሰዎች ላይ ሊተስዋሉ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
• እራስን እስከማጥፋት መሞከር

#ህክምናው

የድባቴ የአይምሮ እክል ላጋጠማቸው የፀረ ድባቴ መድኃኒቶች የሚሰጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በአእምሮ ሀኪም እና ከስለ ልቦና ባለሞያ የንግግር ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከድብርት እና ከጭንቀት መሰል ከአእምሮ ውጥረቶች ለመላቀቅ እና ለመረጋጋት እንደሚረዳ በዘርፉ ባለሞያዎች ዘንድ ይነገራል፡፡ እንዲሁም በተቻለ አቅም ሰዎች ከአሉታዊ ይልቅ አውንታዊ ሃሳቦች ላይ ተኩረት እንዲያደርኩ ይመከራል፤ ይህም ከድባቴ እዲላቀቁ እና የደስተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply