ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድባቸው የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎችን ይፋ ሆኑ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ ድጋሚ እንዲካሄድባቸው የተወሰነባቸውን የምርጫ ክልሎችን ይፋ አደረገ፡፡በዚህም ባስኬቶ ልዩ ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣ ቡሌ ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ጉመር 2 የክልል ምክር ቤት ፤መስቃና ማረቆ ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ቦርዱ በተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች መስከረም 20 ቀን 2014 ድምጽ አሰጣጥ እንደሚከናወን ገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply