
በክልሎች ሥር ተዋቅረው የሚገኙትን ልዩ ኃይሎች በፌደራል እና በክልል የመከላከያ እና የፀጥታ መዋቅር ውስጥ እንዲካተቱ እንደሚደረግ ከተነገረ በኋላ የድጋፍ እና የተቃውሞ ሃሳቦች ከተለያዩ ወገኖች ሲሰነዘር ቆይቷል። ይህንን ክልሎች በወታደራዊ ደረጃ የሰለጠነ እና የታጠቀ ልዩ ኃይል ማዋቀራቸውን በተመለከተ ከሕግ አንጻር ያለውን አንድምታ በመጥቀስ ክርክሮች ሲካሄዱ የነበረ ሲሆን፣ አስፈላጊነቱም ጥያቄ ሲነሳበት ነበር። አሁን መንግሥት ልዩ ኃይሎችን በሚመለከት የመልሶ ማዋቀር እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።
Source: Link to the Post