ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ባንክ የሂሳብ ደብተር እንዳላቸው ኒው ዮርክ ታይምስ አጋልጧል፡፡

ፕሬዝደንት ትራምፕ የባንክ የሂሳብ ደብተሩን ከፍተዋል የተባለው ለትራምፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ማኔጅመንት ሲሆን ከ2013 እስከ 2015 ድረስም አሰፈላጊው ግብር እንደተከፈለበት ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በምርመራ ዘገባዬ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የአሜሪካ ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ ቻይና ማዞራቸውን በእጅጉ ሲቃወሙ የነበሩት ትራምፕ እርሳቸው በዚያ የባንክ የሂሳብ ደብተር እንዳላቸው መሰማቱ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ቃል አቀባያቸው ነገሩ እንደታሰበው እንዳልሆነ ተናግረው ከዚያ ይልቅ በእስያ የሆቴል ስራ አቅም እንዳለ ለማወቅና ወደዚያም ለመሰማራት የሚያስችል ጥናት ለማድረግ የተከፈተ ነው ብሏል፡፡

ትራምፕ በቻይና የንግድ ሥራ በሚሠሩ የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ትችት ሲሰነዝሩ ይደመጣል ከቅርብ ጊዜያት በኃላም በሁለቱ አገራት መካከል ቀዝቃዛ የንግድ ጦርነትም ተቀስቅሷል ፡፡

የግል እና የኩባንያው የፋይናንስ ዝርዝሮችን ያካተተውን የትራምፕ የግብር መዝገቦችን ካገኘ በኋላ ነበር ኒው ዮርክ ታይምስ ሂሳብ ደብተሩን ያጋለጠው ፡፡

ትራምፕ በ2016 እና በ2017 ለፌዴራል መንግስቱ የከፈሉት የገቢ ግብር 750 ዶላር ብቻ መሆኑን ኒው ዮርክ ታይምስ ማጋለጡ የሚታወስ ነው።

አሁን አለ የተባለው ይህ ትራምፕ በቻይና የተከፈተው የሂሳብ ደብተር 188 ሺ ዶላር ግብር ተከፍሎበታል ተብሏል።

ትራምፕ ተቀናቃኛቸው ባይደንን ለቻይና ይራራል እንዲሁም የቻይና አሻንጉሊት ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ሲተቹ ይደመጣል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply