ዶናልድ ትራምፕ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በመቃወም በኢንተርኔት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

ዶናልድ ትራምፕ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በመቃወም በኢንተርኔት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈርሰዋለች የሚል አሉታዊ አስተያየት መስጠታቸውን በመቃወም ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ በብይነ መረብ ማሰባሰብ መጀመሯን ይፋ ተደርጓል።
የፊርማ ማሰባሰቢያ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተካሄዷል።
የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰቢያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት በበላይነት የሚመራው መሆኑ ተነግሯል።
የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰቢያ ላይ ኢትዮጵያውያን እና በየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ወዳጆች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
በመጪዎቹ ሶስት እና አራት ቀናት ከ100 ሺህ በላይ የተቃውሞ ፊርማ ለማሰባሰብ እቅድ እንደተያዘ ነው የተነገረው።
በፈትያ አህመድ

The post ዶናልድ ትራምፕ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በመቃወም በኢንተርኔት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Yaregal
    Yaregal

    @iyoba4u በቃ መንግስታችን አክቲቪስት ሆኖት አረፈ?

Leave a Reply