ዶክተር አብይ አህመድ ለምን ሀገር ማረጋጋት ተሳናቸው? (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም)   ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ የህወኃት  አገዛዝ በአካል…

ዶክተር አብይ አህመድ ለምን ሀገር ማረጋጋት ተሳናቸው? (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ የህወኃት አገዛዝ በአካል…

ዶክተር አብይ አህመድ ለምን ሀገር ማረጋጋት ተሳናቸው? (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ የህወኃት አገዛዝ በአካልም ሆነ በአመለካከት የተቀበረ መስሎት ነበር፡፡ የህወሓት አመለካከት ኢህአዴግን ተሻግሮ የብልፅግና አስኳል ይሆናል ብሎ ማን አስቦ ነበር? ከጥቂቶች በስተቀር ብዙኃኑ በዶክተር አብይ አህመድ አንደበት ከእሳት እንደገባ ቂቤ ቀልጦ ነበር፡፡ በሻሸመኔ ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ ወላይታ በሀዋሳ ሲጨፈጨፍ፣ በቡራዮ ጋሞ እልቂት ሲፈፀምበት ፣20 ባንክ ሲዘረፍ፣ ኦነግ ወለጋን ሲቆጣጠር፣ ንግድ ባንክ ሲመዘበር ወዘተ የለውጡ ጅማሬ ስለሆነ ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ የችግሩ መዘዝ አኩራፊው ህወኃት ነውም ተባለ፡፡ ደካማው አመራር ሁሉ ህወኃት ሲያለቀልቅ ኑሮ ህወሓትን በመስደብ …በብልፅግና ተሾመ፡፡ ብልፅግናም ያረጁ ህወኃቶች ማህበር ሆነ፡፡ ወጣቱ ዶክተር አብይ ለምን ሀገር ማረጋጋት ተሳናቸው ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ነጥብ ማንሳት ይቻላል፡፡ 1) ራሳቸውን ንጉስ ለማድረግ፣ ባሪያ የሚሆናቸው አመራር ብቻ ማስጠጋታቸው፡፡ 2) የሀገሪቱን ውስብስብ ችግር በምክር እና በቅብ አንደበታቸው ለመሻገር መሞከራቸው 3) ህግ እና ተቋም ከማበጀት ይልቅ ራሳቸውን ዘውዳዊ አድርገው ፣ራሳቸው ብቻ ተቋም መሆናቸው፡፡ 4) ህወኃት የመጣበትን መንገድ አንድም ሳይቀይሩ በአሮጌው መንገድ መጓዛቸው፡፡ 5) ወጥ እና ዘላቂ አቋም አለመኖራቸው 6) ታይታን መውደዳቸው 7) የሀገሪቱን ተቃርኖ የሚፈቱበት ስልት አለመንደፋቸው እና በደመነፍስ መመራታቸው 8) የአማራ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሰነፍ መሆናቸው ዶክተር አብይን አዳክሟቸዋል፡፡ 9) የኦሮሚያ ብልፅግና አይጠግቤ ፍላጎት እና ተለጣጭ ትርፍ ፈላጊነቱ ዶክተር አብይን በሌላው ብሄር ዘንድ ጥርጣሬ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ 10 ) የአዲስ አበባን ጉዳይ የያዙበት መንገድ ተረኝነት የሚያሳይ እና መስፋፋትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ዶክተር አብይ እንደ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ መሪ ለመታየት አስቸግሯቸዋለል፡፡https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply