ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት የጥፋት ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ዶክተር አዲሳለም በፀረ-ሰላም ቡድን ተደራጅተው በመስራት ተጠርጥረው ፍረድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበት ዘመንም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም የመንግስት መረጃና ሚስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።

ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስረድቷል።

የተጠርጣሪው ጉዳይ በችሎት እየታየ ይገኛል።

ታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply