ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ መታሰራቸዉ ተሰማ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አብን ) የመጀመርያው ሊቀመንበር እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አበል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ትናንት ምሽት በፀጥታ አካላት ከቤታቸው ተይዘው መታሠራቸው ተገለፀ።

የዶክተር ደሳለኝ ቤተሰብ መሆናቸውን የገለፁ ሰው ለዶቼ ቬለ እንዳሉት የምክር ቤት አባሉ ትናንት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ አዲስ አበባ ውስጥ ከመኖሪያ ቤታቸው አምስት በሚደርሱ የፀጥታ አካላት “በሕግ ትፈለጋለህ” በሚል ተይዘው መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

አብን ከተመሠረተ ጀምሮ በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እስካስረክቡበት ወቅት ድረስ የፓርቲው የመጀመርያው ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተወከሉ ጥቂት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት መካከል አንደኛው ናቸው።

በፓርላማው ውስጥ አነጋጋሪ ሀሳቦችን ከሚያነሱ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም ቤታቸው መበርበሩን እና በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን ከቤተሰባቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply