You are currently viewing ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አስገራሚ ሀሳቦችን አንስቷል። ግልፅ ስጋቶች አሉብን ብሏል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ። ስጋቶቹ ድርድሩን የተመለከቱ ናቸው። ጥቅምት 2…

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አስገራሚ ሀሳቦችን አንስቷል። ግልፅ ስጋቶች አሉብን ብሏል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ። ስጋቶቹ ድርድሩን የተመለከቱ ናቸው። ጥቅምት 2…

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አስገራሚ ሀሳቦችን አንስቷል። ግልፅ ስጋቶች አሉብን ብሏል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ። ስጋቶቹ ድርድሩን የተመለከቱ ናቸው። ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የፌዴራል መንግሥቱ ወይም ብልፅግና የሚመራው መንግሥት የአማራን ሕዝብ ጥቅሞች በሙሉ ልብ ይዞ ይሳተፋል የሚል እምነት የለንምያለው ዶክተር ደሳለኝ፡፡ እኛ ብቻ አይደለንም ሕዝባችንም ይህ ነው እምነቱ ብሏል።፡ አንደኛ ዛሬ ብልፅግና በሚባለው ፓርቲ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር ሆነው የምታያቸው እኮ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር ሆነው ብአዴን በሚባለው ድርጅት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬም የድርድር ቡደኑ አባል ሆነው የተካተቱት ሰዎች እኮ ትናንት ወልቃይት ወደ ትግራይ ሲከለል፣ ራያ ወደ ትግራይ ሲከለል፣ ወፍላ ወደ ትግራይ ሲከለል ይከለል ብለው የወሰኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እኛ ዋነኛ ተዓማኒነታቸውና ተጠሪነታቸው ለፓርቲያቸው እንጂ ለሕዝባቸው ነው ብለን አናምንም፡፡ ነገር ግን ሁሉም እዚያ ውስጥ ያለ አካል ተቆርቋሪ አይሆንም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ግልጽ የሆኑ ሥጋቶች አሉን፡፡ እነዚህ ሥጋቶች ደግሞ ዝም ብለን አየር ላይ ያሉና በግምት የፈጠርናቸው ሳይሆኑ፣ በተጨባጭ ባለፉት ዓመታትና ባለፍንባቸው ታሪኮች የሚነሱ ጉዳዮች ስለሆኑ መነሳት አለባቸው፡፡ ሁለተኛ የፌዴራል መንግሥት አማራ ክልልን ይወክላል ከተባለ፣ የፌዴራል መንግሥት ትግራይንም ይወክላል እኮ፡፡ ትግራይ እስካሁንም የፌዴሬሽኑ አባል ነው፡፡ በእኛ በኩል የምናስበው የፌዴራል መንግሥት እንደ መንግሥትነቱ ወደ ድርድር ይዟቸው የሚቀርቡ የድርድር ነጥቦች አሉ፡፡ በዚህ ጦርነት ውስጥ ደግሞ በተለየ ሁኔታ ከሌሎች ክልሎች በተለየ የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎች በጦርነቱ ውድመት የተፈጸመባቸው ናቸው፡፡ ያ ማለት ሁሉም ኢትዮጵያዊ አልወደመም ማለት አይደለም በዚህ ጦርነት፡፡ ነገር ግን በተለየ ሁኔታ ከጦርነቱ መሠረታዊ መነሻ ጉዳዮች አንዱ የማንነትና የታሪክ በመሆኑ፣ እነዚህ ደግሞ በተለየ ሁኔታ በአማራና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ስለነበሩ፣ በዚህም እኛ ጠብቀነው የነበረው የአማራ ክልል መንግሥት ራሱን ችሎ ለድርድር ይቀርባል ብለን ነበር፡፡ የፌዴራል መንግሥት ደግሞ በፌዴራል መንግሥቱ የሥልጣን ገደብ ልክ፣ እንዲሁም በሕወሓት በኩልም የራሳቸውን ፍላጎት ይዘው ይቀርባሉ የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን የአማራ ክልል መንግሥት ያንን ጥያቄ አላቀረበም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት ያን ጥያቄ አላቀረበም ማለት የአማራ ሕዝብ ወኪሎች ወይም ድርጅቶች ዝም ብለው ይቀመጣሉ፣ ዝም ብለው ሒደቱን ይመለከታሉና ሌሎች በ1983 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሕዝብ ዕጣ ፈንታ ላይ ወስነው የፌዴራል ሥርዓቱን እንደጫኑት ዝም ብለን እናያለን ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ አማራ በታሪክ ሌላ አካል ወስኖ እንዲቀበል የተደረገበት ሒደት አሁን ላይ አይሠራም፣ ልጆቹ ተደራጅተዋል፡፡ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጠንካራው የአማራ ሕዝብ ላይ ማንም ተወያይቶ ፍላጎቱን እንዲጭንበት አይፈቅዱም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከሁሉም አደረጃጀቶች የተውጣጣን ልጆች ዛሬ የምናደርገው ትግል ለአማራ ሕዝብ ወሳኝ የታሪክ መታሰቢያ አድርገን ልናየው እንችላለን፡፡ ይህንም በዚህ ደረጃ አማራ በእኔ ጉዳይ፣ በእኔ ፍላጎት፣ በእኔ መብት እኔ እንጂ ሌላ ማንም ሊወስንብኝ አይገባም ብሎ ወደፊት መውጣቱ የሕዝባችን የትግል እመርታ የሚያሳይ አድርጌ እወስደዋለሁ ሲል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ሀሳቡን ለሪፖርተር ጋዜጣ አጋርቷል። ……………….. ዘገባው የሳተናው ሚዲያ ነው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply