
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶክተር ድረስ ሳኅሉ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡
ዶክተር ድረስ ሳኅሉ የተሾሙት በቀድሞው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መሐሪ ታደሰ ምትክ ነው፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት የ4ኛ ዙር ምርጫ የ8ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤው ማካሄዱን ተከትሎ ነው የዶክተር ድረስን ሹመት ይፋ ያደረገው፡፡
ምክር ቤቱ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ በሥራቸው ጠንካራና በትምህርት ዝግጅታቸውም አቅም ያላቸው ናቸው ማለቱን አብመድ ዘግቧል፡፡
The post ዶክተር ድረስ ሳኅሉ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post