ዶ/ር ሂሩት በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ዶ/ር ሂሩት በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

ሚኒስትሯ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየውን ታሪካዊ ግንኙነት አስታውሰው ይህንን ታሪካዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ማስቀጠል  ይገባል ብለዋል።

በተለይ በባህል፣ በቱሪዝምና በስፖርት መስክ ከፈረንጆቹ 2001 እና 2010 የተደረጉትን የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶች

እንደገና ማደስ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቷል።

በቅርቡም ረቂቅ የጋራ መግባቢያ ሰነድ አዘጋጅተው እንደሚልኩ እና እንደሚፈረም የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post ዶ/ር ሂሩት በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply