ዶ/ር ሊያ ታደሰ የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 16 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ሆስፒታሉ የእስካሁን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የተመዘገቡ ጠንካራ ውጤቶችን በማስመልከት ሆስፒታሉ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥ አድማሱን ማስፋት በሚችልበት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ሆስፒታሉ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮምሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ደረጃን ያገኘ ሆስፒታል ነው ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት 389 አልጋዎችን በመያዝ ለስልጤ ዞንና ሌሎች በሀገሪቱ ለሚገኙ 5 ሚሊየን ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለው ከስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

The post ዶ/ር ሊያ ታደሰ የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply