ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰየሙ

ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ህዳር 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሰየማቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡

በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ  ይታወሳል::

ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ እንደገለፁት በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ሆነው፣ የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል ይሾማሉም ብለዋል ፡፡

The post ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰየሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply