ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ አገለሉ

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ አገለሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ ማግለላቸው (ኩዋራንቲን) ማድረጋቸው ተገለፀ።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በቅርበት ያገኙት ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ስለተረጋገጥ ራሳቸውን ለብቻ አግልለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ አንደሚገኝ እና ምንም አይነት የቫይረሱ ምልክት እንደሌለባቸውም አስታውቀዋል።

ሆኖም ግን በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ለቀጣይ ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ ያስታወቁት ዶክተር ቴድሮስ፥ ስራቸውንም ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

The post ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ አገለሉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply