ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ተመርጠዋል፡፡በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/WoVDk-6Kmvv8HwKAqcnLljpJPd75kt4Q-9GAuF3b0bjasjz43v6TflSJI2pEPPEG5AeA5LWq_ow_66bOWRAI1eOSEqaWyKJRgIlAVmkW5S6a04Wb8uldusE6Sw0hSeYUSkRyojyeFRmT5ykzWXS5lskFKjGNu0nDkCXEdCFj44NFJMbIBkQBbYGd_f7sNNdn8neMzVlKbSJtQ_v2qjjHhK_wMaYoze69J_FvAbSI4TUR3CuFN_7-etM8YCXmWmJfZ6C6D_hd-0QrEPDLML9Sm0mtMFRrymnQwgdVdSoPwzp1ZE_6iJHRQ8cTE2IYu0aFksq6JdyM8LjDwMWH2I_a1A.jpg

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ተመርጠዋል፡፡

በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው ተረጋግጧል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ ላለፉት አምስት ዓመታት የተባበሩት መንግሥት ጤና ድርጅት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን በዚህ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭት እና ተቋማቸው ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የገባው ውዝግብ የሥልጣን ዘመናቸውን ፈታኝ አድርጎባቸዉ እንደነበር ይነገራል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ መመረጣቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “በእኔ ላይ ላላችሁ መተማመን እና ለጣላችሁብኝ እምነት አመሰግናለሁ” ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ተቋሙን በይፋ ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለሁለተኛ ዙር መምራት ይጀምራሉ መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply