ዶ/ር ቴድሮስ የቀረበባቸውን ክስ ማስተባበል

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በወቅታዊው ወታደራዊ ግጭት ከሕወሓት ጋር ወግነዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ አስተባበሉ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ ከሰሞኑ ‹‹ለሕወሓት ትጥቅ ለማስገኘት በሚል እና ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ላይ ጫና እንዲያሳድር በማሰብ ሲያሴሩ ነበር›› በሚል በመገናኛ ብዙሃን ስማቸው ሲብጠለጠል ሰንብቷል፡፡

በሙከራቸውም ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረዋል በሚል በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲወቀሱም ነበር፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላም ኅዳር 9 በሰጡት መግለጫ ዶክተር ቴድሮስ ከሕወሓት ጋር እየወገኑ መሆናቸውን ማንሳታቸው ደግሞ በርካቶች ቅር እንዲሰኙ አድርጓቸዋል፡፡

‹‹ከኢትዮጵያ ሰዎች ጋር ወግኖ እነዚህን ሰዎች ያወግዛል ብለን አንጠብቅም፤ እነሱን ለመርዳት ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም፤ ጎረቤት አገራት ሳይቀር ቀስቅሷል፤ ጦርነቱን ተቃውሞ አውግዙ ብሏል፡፡ እንዲሁም ጦር መሳሪያ እንዲያገኙ ሰርቷል›› ሲሉ ነው ጄኔራል ብርሃኑ ዶክተር ቴድሮስን የከሰሱት፡፡

ዝምታን መርጠው የሰነበቱት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ታዲያ ኅዳር 10 ሌሊት በትዊተርና የፌስ ቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹በተፈጠረው ሁኔታ ለአንድ ወገን እንደወገንኩ ተድርጎ የሚወራው ነገር ሃሰት ነው እንዲታወቅ የምፈልገው ውግንናዬ ከሰላም ጎን ብቻ ነው›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply